=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
እውነት ሙስሊም ወጣቶች ዳእዋ ማድረግ ይችላሉን? አዎ ይችላሉ!!!
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው!
የአሏህ ሰላምና እዝነት በነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) እና በቤተሰቦቻቸው እንዲሁም የሳቸውን ፈለግ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።
ለምንድነው እኛ ሙስሊም ወጣቶች ጓደኞቻችን ወደ አሏህ ቅርብ ይሆኑ ዘንድ የማንረዳቸው? በኢስላም ላይ ጥላቻ ያላቸው አስተማሪዎች ሶላታችነን እንዳንሰግድ ለማድረግ ከላይ ከታች ለሚሉ ሰዎች ፣ ሂጃብ ኋላቀርነትና ጭቆና ነው ለሚሉ ፣ በየሃይስኩሉ ፣ በየዩንቨርስቲው ላሉ ፀረ-ኢስላም አስተማሪዎች እና ፂማችነን ስላሳደግን የረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ሱናን አጥብቀን ስለያዝን ስም ለሚለጥፉልን ሰዎች ሁሉ ቆምብለን ምላሽ ልንሰጣቸው ይገባል። እንዲሁም ሌሎች ለሚገጥሙን ፈተናዎች ሁሉ መልስ ለመስጠት እራሳችነን በእውቀት ፣ በጥበብ እና በማራኪ የአነጋገር ለዛ ልንክን ይገባል።
ኢስላም የግለኝነት እምነት ወይም ለጥቂቶች ብቻ ተጠብቆ የኖረ ሃይማኖት አይደለም። እኛ ሙስሊም ወጣቶች ይህ ዲን እንዲስፋፋ ለማድረግና በዲኑ ጠንካራ የሆነ ትውልድ ለመፍጠር ትልቅ ሚና ልንጫዎት ይገባል። የልጅነት ጓደኞቻችን እነማናቸው? የትኞቹ ጓደደኞቻችን ናቸው የጁምአ ሶላትን መስጅድ ሳይሆን አልባሌ ቦታ የሚያሳልፉ? በክላሳችን ስመ ሙስሊም የሆኑ ጓደኞቻችን እነማናቸው? ከአቻዎቻችንና ከጓደኞቻችን ጋር የመግባባት እና የመረዳዳት እድሉ አለን ስለዚህ እነዚህ ሙስሊም ወንድሞቻችነን እና እህቶቻችነን ከአሏህ ጋር ያላቸው ትስስር ጠንካራ እንዲሆን ለጌታቸው ትእዛዝ የራሳቸውን ፍላጐት መስዋእት የሚያደርጉ እንዲሆኑ በቀጥታም ሆነ በተዘዋሪ መንገድ ወደ ኢስላም ጥሪ ማድረግ ይኖርብናል። ይህን ለማድረግ ቀዳሚ የሚሆነው የራሳችነን ስብእና ማስተካከልና በነፍሶቻችን ላይ መዝመት ነው። በቅድሚያ እራሳችነን የተግባር ሰው ልንሆን ግድ ይላል ፤ ይህን ባደረግን ወቅት የኢስላም አስተምህሮት በራሳችን ላይ ይንፀባረቃል ፤ ይህ ሆነ ማለት በሌላ አገላለፅ ጥሪ የምናደርግላቸው ነገሮች በቀላሉ ተቀባይነትን እንዲያኙ አደረግን ማለት ነው።
1) ቅን የሆነች ኒያን እናድርግ
በመሠረቱ ስራዎቻችን ሁሉ ለአሏህ ብለን የምንሰራቸው መሆን ይኖርባቸዋል ፤ ይህም ወደ ኢስላም የምናደርገውን ጥሪ ያጠቃልላል። ይሁንጂ እራሳችነን እንደ አስተማሪ በመቁጠር ስራዎቻችን ከእብሪተኝነት ጋር የተያያዙ መሆን አይኖርባችውም።
2) ለምንሰብከው ነገር በፅሁፍም ይሁን በንግግር ቅድሚያ እራሳችነን የተግባር ሰው እናድርግ። እኛ የማናደርገውን ነገር ሰዎችን መስበክ ትክክል አይደለም።
3) ቁርአንን እና ሐዲስን ብቻ እንደ መመሪያነት እንጠቀም። ከሁሉም ነገር በላይ ተወዳጅ የሆኑት ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የኢስላምን መልእክት ለሕዝቦቻቸው እንዴት ያስተላልፉ እንደነበር የሚያወጉ የቁርአን አናቅፅቶችን እና ሐዲሶችን አንብበን በጥልቅ መረዳት ይኖርብናል። ይህን ለማድረግ ቁርአንን በአረብኛ ቇንቇ መረዳት ባንችል ቢያንስኴ ልንረዳ በምንችለው ቇንቇ የተተረጐመ ቁርአን እናንብብ ፣ እንረዳ ፣ እንወቅ። የሲራ መጽሐፍቶችን አገላብጠን እናንብብ።
4) ለሰዎች ቅርብ እንሁን
ሰዎችን በመመልከት ማንነታቸውን እናቃለን ብለን አንሰብ። በየዩንቨርስቲዎቻችን ሶላት ላይ የማይገኙ ወጣቶች መጥፎ ሙስሊሞች ሊመስሉን ይችሉ ይሆናል ፤ ምናልባት ስለ ኢስላም የማያውቁት ነገር ቢኖርስ።
እራሳችነን ማህበራዊ እናድርግ። በዚህ ዙሪያ በየሃይስኩሎቻችን በየዩንቨርስቲዎቻችን እና በየሰፈሮቻችን እየተስተዋለ ያለው ትልቁ ችግር እራሳችነን ከማህበራዊ ኑሮ ይልቅ ግለኝነት የተሞላበት ሂወትን መምረጣችን ነው። እስኪ በየሃይስኩሎችም ይሁን በየዩንቨርስቲው ከሙስሊሙ ጀምአ ጋር ጠንካራ ትስስር ያለን ስንቶቻችን እንሆን? በጀምአዎቹ ከሚደረጉ ኢባዳዎች ውስጥ በንቃት እየተሳተፍን ያለን ስንቶቻችነን? በየሰፈራችን ያሉ ሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር ለተወሰነ ደቂቃ ቁጭ ብለን ስለ ዲናችን ፣ ማህበራዊ ኑሮአችን ባጠቃላይ ስለ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እየተወያየን ያለን ስንቶቻችን እንሆን? አደለም ቁጭ ብለን ስለ ወቅታዊና አንገብጋቢ ጉዳዮቻችን መወያየት ቀርቶ ሙስሊም ወንድሞቻችነን እና እህቶቻችነን በመንገድ ላይ ስናገኛቸው ሰላምታን የምንለዋወጥ ስንቶቻችን እንሆን? ሰላምታን መለዋወጥ እፍረት እየሆነብን አይደለምን? እስኪ በዙርያችን ያሉ ሰዎች ጋር ያለን ማህበራዊ ትስስር ምን እንደሚመስል እንመልከት።
5) ፈገግተኛ እንሁን
ፈገግተኝነት ፣ ትሁትነት እና ደግነት ሁልግዜም ልንተገብራቸው የሚገቡ የረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ባህርያት ክፍሎች ናቸው። ሌሎችን ለመቅረብ እራሳችነን ማህበራዊ ለማድረግ ብዙ መልፋት አይጠበቅብነም ፤ ዋናው ነገር አእራሳችነን ቅርብ ማድረረግ ነው ፤ ለዚህም ቁልፉ ፈግገግተኝነትና ሰላምታን የሚያበዛ መሆን ነው። እዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባ ነገር ቢኖር ለሰዎች ቅርብ መሆን ማለት እራሳችነን ከተቃራኒ ፆታ ጋር እንቀላቀል ማለት አይደለም። ለዚህም ኢስላም የራሱ የሆነ ህግጋት አለው ፤ ሁላችነም ይህን ህግጋት ልንከተል ግድነው።
6) አዳዲስ ሃሳቦችን የማመንጨት ክህሎት ይኑረን።
7) ኢስላም አስፈላጊ እና ሙሉ የሆነ የሂወት መመሪያ መሆኑን እናሳያቸው።
• በመጀመሪያ እራሳችን ጥሩ ተምሳሌት ልንሆን ይገባል።
• ዳእዋ ከማድረጋችን በፊት ኢስላምን ሙሉ በሙሉ የሚከተል የተግባር ሰው መሆን ይጠበቅብናል።
• ዳእዋ ለምናደርግላቸው ሰዎች ከነሱ በላይ መሆናችነን በቀጥታም ይሁን በተዘዋሪ ልናሳይ አይገባም።
• የሌሎችን ሃይማኖት መዝለፍ ፣ ማርከስ አይኖርብነም።
• ሶብርና የመንፈስ እርጋታ ይኑረን።
• ዳእዋ በምናደርግ ጊዜ ትክክለኛ የሆነ የአካል እንቅስቃሴ እና ያማረ የአነጋገር ለዛ ይኑረን።
• የመልካም ባህርያት እና ስብዕና ባለቤት እንሁን።
• ረጋ ባለ አነጋገር ፣ ታላቅ እና ቁልፍ በሆኑ ቃላት ኢስላም ምን ያህል ውብ እንደሆነ ግልፅ እናድርግላቸው።
• እነዚህን ባህርያቶች መላበሳንችን ዳእዋ የምናደርግበትን መድረክ ይፈጥሩልናል።
• መፅሐፎችን ገዝተን ወይም አንብበን የጨረስናቸው ካሉ በስጦታ መልክ እናበርክት።
«ላኢላሃ ኢለሏህ» የሚለውን አረፍተ ነገር አውቀህ ለሌሎች ማስተላለፍህ ላንተ ዳዕዋ ነው!!!
Δ በማህበራዊ ኑሯችን ያሉ አጋጣሚወችን በመጠቀም
۵ ስራችን ከቤታችን መጀመር ስላለብን ከቤተሰቦቻችን ጋር ስለዲናችን የምንነጋገርበት ሰአት በማመቻቸ
۵ ለታናሽ ወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን ስለ ኢስላም ያላቸውን ግንዛቤ ለማስፋት መሞከር
- እንዴት ለሚለው
የምናውቀውን ነገር በማሳወቅ
- መፅሃፎችን ገዝተን በመስጠት
- ኪታብ የሚቀሩበትን ሁኔታ በማመቻቸት
- በመልካም ስራዎች ሁሌም እኛ ጋር እንዲሳተፉ በማድረግ ወ.ዘ.ተ
۵ ከጓደኞቻችን ጋር ቁጭ ስንል ስላነበብ ነው ወይም ስላዳመጥነው ነገር መነሻ ሃሳብ በማቅረብ መወያየት
Δ ሚዲያዎችን በመጠቀም
۵ ኢስላማዊ ፅሁፎችን እና ፎቶዎችን በማዘጋጀት በማህበራዊ ድህረ ገፆች ፖስት በማድረግ ወይም ሌላ ሰው ያዘጋጃቸው ካሉ በውስጣቸው ያለውን ይዘት ከገመገምን ቡኋላ ሼር ማድረግ
۵ ሳምንታዊ ወይም ወርሃዊ የሆኑ አጭር የሐዲስና የቁርአን አናቅፅቶችን ለሚያውቇቸው ሰዎች በሜሴጅ መላክ
۵ ልዩ በሆኑ ቀናቶች ለምሳሌ በጁምአ ፣ በሁለቱ ኢዶች በራሪ ወረቀቶችን በማዘጋጀት መበተን
۵ አንብበን የጨረስናቸው መፅሐፎች ካሉ በውሰት ወይም በስጦታ መልክ ማበርከት
Δ ሚዲያዎችን በመፍጠር
- የሞባይል ዎብሳይቶችን በመፍጠር
- ፔጆችንና ግሩፖችን በመክፈት
- ቻት ግሩፕ በማዘጋጀት
websites:
http://youth-mission.mobie.in
http://youth-mission.blogspot.com
fb page:
http://facebook.com/youth.mission29
'~'-.,__,.-'~'
_,.-'~''~'-.,_
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|